Fana: At a Speed of Life!

በማርች ባንድ፣ ኦርኬስትራና ቴአትር ሙያ የሰለጠኑ የፖሊስ አባላት ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29 ፣2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በማርች ባንድ፣ ኦርኬስትራና ቴአትር ሙያ ያሰለጠናቸውን 128 የፖሊስ አባላት አስመረቀ።
ፖሊስ ኮሚሽኑ በማርች ባንድ፣ ኦርኬስትራና ቴአትር ሙያ የፖሊስ አባላትን አሰልጥኖ ሲያስመረቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
ስልጠናው ከፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የተሰጠ ሲሆን፥ የፖሊስ አባላቱ እንደየ ሙያ መስካቸው ከ7 እስከ 14 ወር ስልጠና መውሰዳቸው ተገልጿል።
በምረቃ መርሃ ግበሩ ላይ የፖሊስ ከፍተኛ መኮንኖችና የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.