ኢሬቻ መልካ አቴቴ ተከበረ
አዲስ አበባ፣መስከረም 30፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢሬቻ መልካ አቴቴ በቡራዩ ዛሬ ተከብሯል፡፡
ኢሬቻ መልካ አቴቴ ኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔና ሆራ አርሰዴ በዓል ከተከበረ በኋላ የሚከበር መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዚህም ዛሬ ኢሬቻ መልካ አቴቴ ቡራዩ በተለያዩ ባህላዊ አልባሳትና በተለያዩ ጣእመ ዜማዎች ታጅቦ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተከብሯል ።
በዓሉ የሠላምና የእርቅ ተምሳሌት እንደመሆኑ ትዉልዱ ሊንከባከበዉና ሊጠብቀው ይገባል ሲሉ የበአሉ ታዳሚዎች አስተያየታቸውን መስጠታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!