ኢትዮጵያዊነት የበጎ አድራጎት ማህበር በጌዴኦ ዞን ለተቸገሩ ተማሪዎች ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊነት የበጎ አድራጎት ማህበር በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ከተማና ወናጎ ወረዳ ለተቸገሩ ተማሪዎች ድጋፍ አደረገ፡፡
ማህበሩ ዋን ፓክ ፎር ዋን ቻየልድ (One pack For one child) በኩል ለማህበሩ በጌዴኦ ዞን ድጋፍ ለሚሹ 650 ተማሪዎች ከ200 ሺህ ብር በላይ በሚገመት ገንዘብ የትምህርት ቁሳቁስ ማበርከቱን ጠቁመው በቀጣይም በተቋም ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ የማህበሩ ሰብሳቢ ወጣት ነብዩ ፍቃዱ አስታውቀዋል፡፡
የይርጋጨፌ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብዮት ጀቦ÷ በከተማ በርካታ ድገፍ የሚሹ ተማሪዎች እንዳሉ ተናግረው ከሁለት ማህበራት በኩል ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎች በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ከመኖር ባሻገር ወላጆቻቸውን ያጡ መሆናቸው ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዳይማሩ ተጽዕኖ መፍጠሩን ጠቅሰው ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን የዞኑ የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!