Fana: At a Speed of Life!

ጽዳት በአመት አንዴ ብቻ ሳይሆን የሁል ጊዜ ተግባር መሆን አለበት- የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጽዳት በአመት አንዴ ብቻ ሳይሆን የሁል ጊዜ ተግባር መሆን እንዳለበት በአዲስ አበባ ከተማ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ገለጸ፡፡

በመዲናዋ በተለያዩ ክፍለ ከተሞችና በሌሎች የሃገሪቱ አካባቢዎች የጽዳት ዘመቻ መርሀ ግብር ተካሂዷል ።

በቦሌ ክፍለ ከተማ በተካሄደው የጽዳት ዘመቻ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ለማን ጨምሮ÷ የክፍለ ከተማ አመራሮች ፣የፀጥታ ኃይሎች ፣በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ፣የጽዳት ሰራተኞች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

ህዳር 12ትን ጠብቆ ደረቅ ቆሻሻን ሰብስቦ ማቃጣል የእኛኑ ሀብት የሚያወድም ተግባር ከመሆኑ ባሻገር አካባቢያችን የሚበክል መሆኑን÷ የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ጽዳት በዓመት አንድ ቀን ብቻ የሚደረግ ሳይሆን በየዕለቱ በምናደርገው የማያቋርጥ ሂደት መከናወን አለበት ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ነዋሪዎች ከተማዋን ፅዱና አረንጓዴ በማድረግ የጀመሩትን ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ዋና ዳይሬክተሩ ማሳሰባቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕረስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ በሀረሪ ክልል “አካባቢያችንን ከቆሻሻ ሀገራችንን ከአሸባሪዎቹ ህውሃትና ሸኔ እናፀዳለን” በሚል መሪ ቃል የፅዳት ዘመቻ የተካሄደ ሲሆን÷ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.