በአሜሪካ ከተሞች የተካሄደው ሰልፍ ዋሽንግተን በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለውን ፖሊሲ እንድታጤነው ያደርጋታል
አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጫና በመቃወም በአሜሪካ ከተሞች የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ዋሽንግተን በአዲስ አበባ ላይ የምትከተለውን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ መለስ ብላ እንድታጤነው ያደርጋታል ሲሉ የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ገለጹ።
በስያትል የሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት ኢንጂነር ሲሳይ አለማየሁ፥ ሰልፉ የአሜሪካን ህዝብ ሀቅን እንዲያወቅ በማድረግ ተጽህኖ ፈጣሪ ተቋማትን ከኢትዮጵያ ጎን ማቆም የተቻለበት ነው ብለዋል።
ከሶስት ዓመት በፊት ኢትዮጵያዊያን በቃኝ ብለው በትግል ከጫንቃቸው ያወረዱትን አሸባሪው ህወሃት አሜሪካ ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግና የኢትዮጵያን መንግስትን ጫና ውስጥ በመክተትእያደረገች ያለውን ጥረት የአሜሪካ ህዝብ እንዲረዳው ለማድረግ ተሞክሯልም ነው ያሉት።
ከዚያም ባሻገር ተጽዕኖ ፈጣሪ እንደብላክ ላይፍ ማተር እና በርካታ የሰብዓዊ መብት ተቋማት በሰልፉ ተወካዮቻቸው እንዲገኙ መደረጉም ከፍተኛ ድል ነው ብለዋል።
ትውልደ ኢትዮጵያዊው የህክምና ባለሙያ ግርማቸው ተፈራ በበኩላቸው ፥ ጆ ባይደንም 1 ሚሊየን ትውልደ ኢትዮጵያዊን አሜሪካዊያን መራጮቻቸው ያሳዘነው አካሄዳቸውን ቆም ብለው እንዲመለከቱ ሰልፉ ያስገድዳል ነው ያሉት።
የህክምና ባለሙያው አያይዘውም ይህ የባይደን አስተዳደር እና የሚከተለውን ፖሊሲ ጥያቄ በመክተት ለቀጣይ ምርጫ ድምፅ ሊያሳጣቸው እንደሚችልም ነው የተናገሩት ።
በብራስልስ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪው ዶክተር ዘሪሁን አሰፋ ፥የህብረቱ አባል ሃገራት ከቆሙበት የዲሞክራሲ መርህ በተጻራሪ ሁኔታ መገኝታቸውን ሰልፉ አሳይቷል ነው ያሉት።
በሚዲያቸው ሀሰተኛ ወሬ እና ፕሮፖጋንዳ በማሰራጨት እያካሄዱት ያለውን ምረዛ እና ሁሉን አቀፍ ድጋፍ የተጋለጠበት ነበርም ብለዋል።
አያይዘውም በረከሰው የአሸባሪው ህወሓት እና ሽኔ ጋብቻ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ እና ሴራ በማጋለጥ የአለም ህዝብ ትክክለኛው ገጽታ አሳይቷል ነው ያሉት ዶክተር ዘሪሁን።
የህብረቱ ተቋማትም ጉዳዩን በጽሁፍ እንዲያውቁት መድረጉም ተጽህኖውን ያጎላዋል ብለዋል።
በበላይ ተስፋዬ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!