ታዋቂው ዩቲዩበር አይሾው ስፒድ የኢትዮጵያ ቆይታ…
አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዩቲዩብ ቻናሉ ከ48 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ተከታይ ያለው ታዋቂ አሜሪካዊው ዩቲዩበር ዳረን ዋትኪንስ ጁኒየር (አይሾው ስፒድ) በትናንትናው ዕለት አዲስ አበባን ጎብኝቷል።
የ21 ዓመቱ ዩቲዩበር በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የጎበኘ ሲሆን÷ በቀጥታ ስርጭት ያስተላለፈውን ጉብኝት ከ260 ሺህ በላይ ሰዎች በቀጥታ ተመልክተዋል እንዲሁም አሁን ላይ ደግሞ የተመልካቾቹ ቁጥር 9 ነጥብ 9 ሚሊየን ተሻግሯል።
ታዋቂ ዩቲዩበሩ በአዲስ አበባ ቆይታው፡-
👉 አዲስ አበባ ሲደርስ የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ አቀባበል አድርገውለታል
👉 የዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየምን በባዶ እግሩ ጎብኝቷል
👉 የተለያዩ ባሕላዊ ውዝዋዜ መሞከር ችሏል
👉 የኢትዮጵያን ቁርጥ ስጋን ጨምሮ የተለያዩ ባሕላዊ ምግቦችን ተመግቧል
👉 በኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የገና ባህላዊ ጨዋታን ተጫውቷል
👉 የኢትዮጵያ ባሕላዊ የሙዚቃ መሳሪያ የሆነውን ማሲንቆ ተጫውቷል
👉 ከአምስቱ እህትማማች አትሌቶች (የዲባባ ቤተሰቦች) ጋር ተገናኝቷል
👉 በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ የኮሪደር ልማቶች እና ፓርኮችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል
👉 በሚስ ወርልድ 2025 የቁንጅና ውድድር ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 2ኛ የወጣችውን ሀሴት ደረጄ ጋር ባደረገው ቆይታ በኢትዮጵያ የተመረተ የሌዘር ጃኬት ስጦታ ተበርክቶለታል
👉 በመዲናዋ የተሰሩ የከተማ ማስዋብ ስራዎችን ለዓለም አስተዋውቋል
👉 የኢትዮጵያን እንግዳ ተቀባይነት በሚሊየን ለሚቆጠሩ ተከታዮቹ አስመልክቷል።