Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ የሚኖሩ ዳያስፖራዎች ሚና የኢትዮጵያን ትክክለኛ መልክ ለማስተዋወቅ…

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ እንዲሰማሩ ከኢትዮ አሜሪካ የንግድ ም/ቤት አባላት ብዙ ይጠበቃል አሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ፡፡

ሰላማዊት ካሳ ከዋሽንግተን ዲሲ እና ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የተወጣጡ የኢትዮ አሜሪካ ንግድ ምክር ቤት አባላትን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ አሁን ያለው የኢትዮጵያ ገጽታ ለተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ምቹ እና ሳቢ ነው፡፡

በተለይ ባለፉት ጥቂት ዓመታት መንግሥት ለቱሪዝም ዘርፉ የሰጠው ትኩረት ዘርፉ የኢትዮጵያን ትክክለኛ መልክ እያሳየ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የንግድ ምክርቤቱ አባላት ሀገራቸውን በአግባቡና ትክክለኛ መልኳን እንዲታወቅ ማድረግ እና ቀርበው መረጃዎችን በማግኘት መስራት እንደሚጠባቅባቸው አንስተዋል፡፡

የምክር ቤት አባላቱ ብሔራዊ የቱሪዝም ብራንድን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራባቸው ስለሚገኙ የመሰረተ ልማት ሥራዎች፣ አዳዲስ የቱሪዝም ፕሮጀክቶችና ያሉትን ሰፊ የኢንቨስትመንት ዕድሎች አብራርተዋል፡፡

ዳያስፖራው በዘርፉ ያለውን ዕውቀት፣ ቴክኖሎጂና ካፒታል ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የቱሪዝም ሆስፒታሊቲ ኢንዱስትሪውን ለማዘመን በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ በንቃት እንዲሳተፍ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የንግድ ምክር ቤቱ አመራሮችና አባላት በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ የታየው ለውጥና አዳዲስ መዳረሻዎች መበራከታቸው ትልቅ መነሳሳት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡

በዘርፉ በኢንቨስትመንት ለመሳተፍና የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሐብት በስፋት ለማስተዋወቅ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸው ÷ ከሚኒስቴሩ ጋር በትብብር ለመሥራት ተስማምተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.