ባንኩ ለአፍሪካ ቀንድ የመንገድ ፕሮጀክት ልማት የ217 ሚሊየን ዶላር ብድር አጸደቀ
ባንኩ ለአፍሪካ ቀንድ የመንገድ ፕሮጀክት ልማት የ217 ሚሊየን ዶላር ብድር አጸደቀ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚገኙ አገራትን በመንገድ ልማት ግንባታ ለማስተሳሰር 217 ሚሊየን ዶላር ብድር ማጽደቁን አስታወቀ።
የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶቹ የሚከናወኑት በኢትዮጵያ በኬንያና በሶማሊያ ሲሆን ÷ መንገዶቹ በሚገነቡበት አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎችንና አጠቃላይ የቀጠናውን አካባቢ ተጠቃሚ እንደሚያደርጉም ተገልጿል።
ከብድሩ 75 ሚሊየን ዶላሩ የተመቻቸው ከባንኩ የልማት ፈንድ ሲሆን ÷ ከወለድ ነጻ እና ቀሪው 142 ሚሊየን ዶላሩ ግን ከባንኩ ወለድ የሚታሰብበት እንደሆነ ታውቋል።
የኬንያ መንግስት 6 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር አስተዋጽኦ ያደረገበትና በ233 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር ከአይሲዎሎ ማንዴራ የሚገነባው 740 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው መንገድ በኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት በማጠናከር ቀጠናዊ ትስስርን ያጎለብታል ተብሏል።
የአፍሪካ ቀንድ አገራትን በመንገድ ልማት ለማስተሳሰር በተወሰደ ተነሳሽነት መሰረት ቅድሚያ ከተሰጣቸው አራት ዋና ዋና የመንገድ ኮሪደሮች መካከል 142 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው እና ከኤል ዋክ እስከ ራህሙ ያለው ፕሮጀክት አንዱ ነው።
በኢትዮጵያ፣ በኬንያ፣ በሶማሊያ፣ በሱዳን፣ በኤርትራና በጂቡቲ መንግስታት የሚመራው ይህ የመንገድ ልማት ፕሮጀክት በአፍሪካ ልማት ባንክ፣ በዓለም ባንክ እና በአውሮፓ ህብረት የሚደገፍ ነው መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!