የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በክልሉ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው – የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በክልሉ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ገለጸ፡፡
የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዋና ዐቃቤ ህግ አቶ አዩብ አህመድ እንደገለጹት ÷ በክልሉ የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ እዝ እቅድ በማውጣት አደረጃጀት በመዘርጋት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።
በተለይም በክልሉ የሚገኙ የፀጥታ መዋቅር በተቀናጀና ሙያዊ ስነ ምግባርን ባከበረ መልኩ ስጋቶችን በመለየት የህዝብን ሰላም ሊያውኩ የሚችሉ ውጥኖችን እያከሸፈ መሆኑን ተናግረዋል።
እየተከናወኑ ባሉ ተግባራትም ተጨባጭ ውጤቶች እየተገኙ መሆናቸውን ጠቁመው ÷ ለዚህም ለሽብር ተግባር ሊውሉ የነበሩ የጦር መሳሪያዎች ፣ የጦር ሜዳ ቁሳቁስ እንዲሁም በርካታ ሞባይሎች፣ ላፕቶፖችና ኮምፒውተሮች ከእነተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ስለመሆናቸው ጠቅሰዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ለሽብርተኞች ሊዘዋወር የታቀደ በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ የያዙ የባንክ አካውንቶችና የባንክ ቼኮች መያዛቸውን፥ በእስካሁኑም ከ100 በላይ የባንክ አካውንቶች መታገዳቸውን ገልጸዋል።
የታገዱት የባንክ አካውንቶች እና ቼኮችም በተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ ድርጅቶች ወጪ ሆኖ አሸባሪዎቹን በገንዘብ ለመደገፍ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ናቸው ብለዋል።
ተጠርጣሪዎችን አስመልክተው ከአሸባሪዎቹ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ አብዛኞቹ ሰዎችም የጦር መሳሪያዎችን ፣ የጦር ሜዳ ቁሳቁስ ፣ የጦር ስልት መረጃዎችን የያዙ ዶክመንቶች ይዘው የተገኙ ናቸው ብለዋል አቶ አዩብ፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞም ያሉ ጉዳዮችን የሚያጣራ የአቃቢያን ህጎችና የመርማሪዎች ቡድን ተቋቁሞ እየተሰራ ነው ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!