Fana: At a Speed of Life!

የአገር ህልውና ዘመቻው ዜጎች የሚፈልጓትን ሀገር እውን ለማድረግ ወሳኝ ሚና አለው – ምሁራን

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እየተካሄደ ያለው የህልውና ዘመቻ ዜጎች የሚፈልጓትን አገር እውን በማድረጉ የቤት ስራ ከፍ ያለ ሚና እንዳለው የዘርፉ ምሁራን ይናገራሉ ፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት እና በሰመራ ዮኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሙክታር ጠይብ፥ የአገርን ህልውና ለማረጋገጥ እየተከናወነ የሚገኘው ዘመቻ የተረጋጋ ፖለቲካ ኢኮኖሚን ለመገንባት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ ተሸንፎ በወጣባቸው አካባቢዎች በሃይማኖት ተቋማት ላይ የፈጸማቸው ጥፋቶች የቡድኑን የጥፋት ተልእኮ በድጋሚ የገለጠ እንደሆነ ረዳት ፕሮፌሰር ሙክታር ጠይብ አስረድተዋል፡፡

ዜጎች በተባበረ ክንድ የአገርን ህልውና ለማረጋገጥ የበለጠ ሊበረቱ እንደሚገባ ያስረዱት በወልቂጤ ዪኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ረዳት ፕሮፌሰር በቃሉ ዋችሶ በበኩላቸው፥ በውጤታማነቱ የቀጠለው አገርን ከጥፋት የመታደግ የህልውና ዘመቻ በቀጣይ ለሚታለመው ጠንካራ የአገረ መንግስት ግንባታ አበርክቶው ከፍተኛ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

የህልውና ዘመቻው የዜጎችን ደህንነት እና እሴቶች ለመጠበቅ ወሳኝ እንደመሆኑ ሁሉም ዜጋ አስተዋጽኦውን ከፍ ማድረግ እንዳለበትም ምሁራኑ አስረድተዋል፡፡

በውጭ የተወሰኑ መንግስታት የተቃጣውን ዘርፈ ብዙ ጫና ለመቀልበስ ብሎም በጫና የማትበገር አገርን እውን ለማድረግ የሚታየውን መነቃቃት በተቀናጀ መንገድ መምራት እና ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በያገባኛል ስሜት መስራት እንደሚጠበቅም ምሁራኑ ጠቁመዋል፡፡

በአወል አበራ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.