Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሬድዋን ለተለያዩ የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ሰጡ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ለተለያዩ የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ሰጡ።

አምባሳደር ሬድዋን ለሴኔጋል፣ ለዚምባብዌ፣ ካሜሩን እና ለኮቲዲቯር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ነው በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ የሰጡት።

በዚህ ወቅትም በወቅታዊ አጋራዊ ሁኔታ፣ በታላቁ የህዳሴ ግድብ እንዲሁም በኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይን አንስተው ተወያይተዋል።

ከሴኔጋሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ባደረጉት ውይይት ሴኔጋል የአፍሪካ ቻይና የትብብር የሚኒስትሮች ፎረምን በማስተናገዷ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.