ከማእድንና ነዳጅ ኩባንያዎች የተሰበሰበ 50 ሚሊየን ብር ለሶማሌ ክልል ተበረከተ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል እየተንቀሳቀሱ ከሚገኙ ማእድንና ነዳጅ ኩባንያዎች የተሰበሰበ 50 ሚሊየን ብር ለሶማሌ ክልል ተበረከተ፡፡
የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ በሶማሌ ክልል እየተንቀሳቀሱ ከሚገኙ የማእድንና ነዳጅ ኩባንያዎች የተሰበሰበ 50 ሚሊየን ብር ለሶማሌ ክልል አበርክተናል ብለዋል፡፡
ገንዘቡ እንደ ትምህርት ቤት እና ጤና ተቋማት ያሉ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ላይ የሚውል መሆኑንም ተናግረዋል ሚኒስትሩ፡፡
ማዕድን የሀገርና የህዝብ ሀብት ነው ያሉት ሚኒስትሩ ዋናው ተጠቃሚ መሆን ያለበትም ህዝብ ነው ሲሉ በፅሁፋቸው አስፍረዋል፡፡
ማዕድን የሚወጣባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎችም ከማእድንና ነዳጅ ሀብቱ በስራ እድልም ይሁን በተለያዩ መንገዶች ተጠቃሚ መሆን ይኖርባቸዋል ነው ያሉት ኢንጂነር ታከለ፡፡
በማእድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ የተመራ ልኡክ ዛሬ ጂግጂጋ የገባ ሲሆን÷ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድና ካቢኔያቸው አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!