Fana: At a Speed of Life!

የሚዛን አማን ፋና ኤፍ ኤም ባልደረባ ጋዜጠኛ ደረጀ ልመንህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 27፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፋና ብድካስቲንግ ኮርፖሬት የሚዛን አማን ፋና ኤፍ ኤም ባልደረባ የነበረው ጋዜጠኛ ደረጀ ልመንህ በ46 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ጋዜጠኛ ደረጀ ባለፉት ስድስት ዓመታት በጋዜጠኝነት ሲያገለግል ቆይቷል።
የሚዛን አማን ፋና ኤፍ ኤም ባልደረባ ከመሆኑ በፊትም በደቡብ ክልል ልዩ ሃይል ፖሊስ አባል የነበረ ሲሆን፥በሚዛን ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በህዝብ ግንኙነት ሙያም አገልግሏል ።
በ1968 ዓመተ ምህረት በቴፒ ከተማ የተወለደ ሲሆን ፥ የቀብር ስነ ስርዓቱም በነገው እለት በሚዛን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የሚፈፀም ይሆናል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በባልደረባችን ህልፈት ጥልቅ ሀዘን የተሰማው ሲሆን፥ ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን ይመኛል።

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.