በጎንደር መንታ ሕጻናት ልጆችን ታቅፈው ድምጽ የሰጡ እናቶች
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መራጮች ድምጻቸውን መስጠታቸውን ቀጥለዋል።
ወይዘሮ ማስተዋል አበራ መንታ ልጆቻቸውን ይዘው በጎንደር ከተማ መድን ምርጫ ጣቢያ ድምጻቸውን ሰጥተዋል።
ወይዘሮ ማስተዋል እንደገለጹት ምንም እንኳን መንታ ልጅ ታቅፎ ለምርጫ መሰለፍ አድካሚ ቢሆንም በምርጫው ድምጻቸውን መስጠት ከግል ድካም በላይ ከፍ ያለ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።
ሌላኛዋ ሁለት ሕፃናት ልጆችን ታቅፈው ድምጽ የሰጡት እናት ወይዘሮ ፀሐይ ረታ ምርጫው ለሕጻናት ልጆቻቸው የሚበጅ፣ ለነገው እጣፋንታ ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ ድምጻቸውን መስጠታቸውን ተናግረዋል።