Fana: At a Speed of Life!

ዩኒሴፍ ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች 13 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች 13 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት የህክምና ቁሳቁስና የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
የዩኒሴፍ አማራ ክልል ማስተባበሪያ ዋና ሃላፊ አቶ አዲሱ ጫኔ፥ ድርጅቱ የህክምና ባለሙያዎችን ተፈናቃዮች ወደ ሚገኙባቸው መጠለያ ጣቢያዎች በመላክ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
 
እስካሁን ለተፈናቃዮች 560 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ መደረጉን ያነሱት ሃላፊው፥ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል።
 
ድጋፉን የተረከቡት የሰሜንሸዋ ዞን ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ ገስጥ ጥላሁን፥ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው የእርዳታ ድርጅቶች ለተፈናቃዮች የሚያደረጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
 
በሳምራዊት የስጋት
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.