በሽብርተኛው ህወሓት ውድመት የደረሰበት ከደብረዘቢጥ ጋሸና ያለው የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና እየተደረገለት ነው
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሽብርተኛው ህወሓት ከፍተኛ ውድመት የደረሰበት ከደብረዘቢጥ ጋሽና ያለው መካከለኛና ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ አስተላለፊ መስመር ጥገና እየተደረገለት መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለፀ፡፡
ጥገናው ከህዳር 24 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ ሲሆን፥ በተካሄደው የመስክ ምልከታም የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑ ታይቷል፡፡
ከደረሱት ጉዳቶች መካከል የመቄት፣ ወድላ፣ አንጎት፣ ጋዞ ፣ ግዳን፣ ደላንታ፣ ዳውንት ወረዳዎችና ሌሎች በአካባቢው የሚገኙ የመካከለኛና ዝቅተኛ የኤሌከትሪክ አስተላለፊ መስመሮች፣ ትራንስፈርመሮች፣ የኮንክሪት ምሰሶዎች፣ ኬብሎችና የሦስት ፌዝ ቆጣሪዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ወድመዋል፡፡
የጋሸና እና የፍላቂት አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ቢሮዎች እና የቢሮ መገልገያ ቁሳቀሶችም ከፍተኛ ወድመት ደርሶባቸዋል ነው የተባለው፡፡
የኤሌከትሪክ አስተላለፊ መስመሮች እና ትራንስፈርመሮች በተጨማሪ ደንበኞች የሚከፍሉበት ወረሃዊ ቢል መክፈያ ሰርቨር፣ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች እና የቢሮ ፋይሎች ከጥቅም ውጪ መሆኑን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የፍላቂት አገልግሎት መስጫ ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ ዩሐንስ ፈንታ÷ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋረጦባቸው የነበሩት ወረዳዎችና ቀበሌዎች ኃይል መልሶ ለማገኛኘት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!