ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሶስት የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር በስልክ ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ከሶስት የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር በስልክ ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ እንዳስታወቁት፥ ከሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል፣ ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ እና ከኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሼኬዲ ጋር ተወያይተዋል።
በስልክ ያካሄዱት ይህ ውይይት ገንቢ መሆኑን በማንሳትም መሪዎቹን አመስግነዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሁለትዮሽ እና አህጉራዊ ግንኙነቶችን ለማጠናከርም እንሰራለን ነው ያሉት።