Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል በሀሪ-ረሱ ሰሙሮቢ ገላአሎ ወረዳ ወረራ በፈፀመበት ወቅት ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈፅሟል

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ሀሪ – ረሱ ሰሙሮቢ ገላአሎ ወረዳ አዳድሌሔንጌግ ቀበሌ አሸባሪው ህወሓት ወረራ በፈፀመበት ወቅት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና የንብረት ውድመት ማድረሱን የወረዳው የአመራር እና የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

የሰሙሮቢ ገላአሎ ወረዳ አስተዳዳሪ ሀሰን ሀንዲ እንደገለፁት፥ የሽብር ቡድኑ በወረዳው ሾልኮ በገባበት ወቅት በንፁሀን ሰዎች ላይ የሰብዓዊ ምብት ጥሰት ፈጽሟል፡፡

በተጨማሪም በጤና ተቋማት፣ በትምህርት ቤቶች፣ በግለሰብ መኖሪያ ቤቶች፣ ድርጅቶች ላይ ከፍተኛ ስርቆት እና ውድመት ፈፅሞል።

የሰሙሮቢ ገላአሎ ወረዳ አካባቢ ነዋሪዎች በበኩላቸው÷ ህወሓት ወረራ በፈፀመበት ወቅት ከፍተኛ የሰብዓዊ ጥሰት፣ የንብረት ስረቆትና ውድመት አድርሷል ብለዋል፡፡

ያሰበውን ዓላማ ሳያሳካ በመደምሰሱ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶናል ሲሉ ተናግረዋል ነዋሪዎቹ።

በዓሊ ሹምባኽሪ

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.