Fana: At a Speed of Life!

በካንሳስ ከተማ የሚኖሩ አሜሪካውያንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን ጫና እንድታቆም አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በካንሳስ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንና አሜሪካውያን የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርገውን ጫና እንዲያቆሙ አሳሰቡ፡፡

ኢትዮጵያውያን እና አሜሪካውያኑ ተቃውሟቸውን ያሰሙት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በካንሳስ ከተማ ተገኝተው ለነዋሪዎች ንግግር ባሰሙበት ወቅት ነው፡፡

ለኢትዮጵያ በጎ አመለካከት ያላቸው የካንሳስ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑት አሜሪካውያንና ኢትዮጵያውያን ፕሬዚዳንት ባይደን በኢትዮጵያ ላይ እያደረሱ ያለውን ጫና በመቃወም ድምጻቸውን አሰምተዋል።

በተቃውሞው ወቅት ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሄኖክ ተከስተ “ከዚህ በኋላ ይበቃል ፤ ምንም ተጨማሪ ጣልቃ ገብነት አንፈልግም ፤ የውክልና ጦርነቱን አሸንፈናል ፤ ምዕራባውያን በተለይም አሜሪካ በእያንዳንዱ ህይወታችን ውስጥ ጣልቃ እየገቡ ነው” ሲሉ አካሄዳቸውን ኮንነዋል፡፡

ሌላዋ ትውልደ ኢትዮጵያዊት ጸደንያ ተስፋዬ ደግሞ ÷ “በቃን” ነፃ የሆነ እና በህዝብ የተመረጠ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ያለን ህዝብ ነን፤ በኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረ ማንኛውም ጣልቃ ገብነት ሊቆም ይገባዋል” ብለዋል፡፡

አሜሪካዊው ጃሰን ዋጎነር በበኩላቸው ÷ “የምንሰማቸው ዜናዎች ሁሉ የሚያስረዱን ሃቅ ቢኖር አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ከፋፋይ የሆነ ፖሊሲ እየተከተለች” መሆኑን ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

አክለውም ÷ “አሜሪካ ይህን የማይረባ ነገር አድርጋለች እና ካሁን በኋላ እንደ ታላቅ አገር ልቆጥራት አልችልም” ብለዋል፡፡

አሜሪካውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ መንግስታቸው በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ እያሳየ ያለውን ጣልቃ ገብነትና አገሪቷን ከአጎዋ የንግድ ትስስር መድረክ ለማስወጣት ያሳለፈውን ውሳኔ መልሶ እንዲያጤን ጠይቀዋል፡፡

ተቃዋሚዎቹ የባይደንን አስተዳደር አሸባሪውን ህወሓት መደገፉን እንዲያቆም እና በኢትዮጵያ ላይ የጣላቸውን ማዕቀቦች እንዲነሳም ነው ያሳሰቡት፡፡

ከዚህ ባለፈም አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እየተከተለች ያለውን የተሳሳተ ፖሊሲ እንደገና እንድትገመግም ጠይቀዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.