የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋሸና ግንባር ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋሸና ግንባር ለሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ በግንባሩ ለሚገኘው የመከላካያ ሰራዊት አመራር አስረክበዋል፡፡
የተደረገው ድጋፍም 48 ሰንዎች፣ 79 ፍየሎች እና 21 ሺህ ሽርጥ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
አቶ ጃንጥራር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሃይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ በጋሸና ግንባር የሰሩት ጀብዱ ለዘላለም ሲዘከር እንደሚኖር አውስተዋል፡፡
በሰራዊቱ ብርታት እና ወኔ ኢትዮጵያ ከፍ ትላለችም ነው ያሉት፡፡
ከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ግንባሮች በመገኘት ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል ያሉት አቶ ጃንጥራር÷ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በምንችል እዘዘው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!