የደሴ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኘች
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ታሪካዊቷ የደሴ ከተማ የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማኔጅመንትና የቴክኒክ ሰራተኞች ባደረጉት ርብርብ ዛሬ ማታ 4:30 ላይ በድጋሚ ኤሌክትሪክ አግኝታለች።
የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከከፍተኛ አመራር ጀምሮ ሁሉም ሰራተኞች ወደ ቀየው የተመለሰውን ህብረተሰብ በጨለማ እንዳይሰቃይና ኑሮው እንዲቀልለት ለማድረግ በትጋት እየሰሩ ይገኛሉ።
በትናንትናው ዕለት ከሚሴ ከተማ ኤሌክትሪክ ማግኘቷን የሚታወቅ ሲሆን፥ የኢንዱስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ ዛሬ ምሽት ያገኘች መሆኗን መገለጹ ይታወሳል።
ነፃ የወጡ ሌሎች አካባቢዎች ላይ የተጎዱና የወደሙ የመካከለኛና ዝቅተኛ መስመሮች የመጠገንና የመገንባት ስራ በመስራት ኤሌክትሪክ እንዲያገኙና ከጨለማ እንዲላቀቁ የማድረግ ስራው ተጠናክሮ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!