Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሰላም ተከብሮ ሕዝቡ በሰላም ወጥቶ እስኪገባ ድረስ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን – ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሰላም ተከብሮ ሕዝቡ በሰላም ወጥቶ መግባት እስከሚችል ድረስ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ሲሉ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ፡፡

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለኢፌዴሪ አየር ኃይል የተለያዩ ድጋፎችን ያበረከተ ሲሆን ÷ ድጋፉን የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሽፈራው አስረክበዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚዋ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የቦሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የሕልውና ዘመቻው ከተጀመረ አንስቶ የአገርን ጥሪ በመቀበልና ለመከላከያ ሠራዊት ደጀን በመሆን በርካታ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው÷ የዛሬውን ድጋፍ ይዘን የመጣነው ‘በርቱ፣ ከጎናችሁ ነን’ ለማለት ነው” ብለዋል።

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት፥ የቦሌ ክፍለ ከተማ ለሠራዊቱ ላበረከተው ድጋፍ አመስግነው፥ “የኢትዮጵያ ሰላም ተከብሮ ሕዝቡ በሰላም ወጥቶ መግባት እስከሚችል ድረስ ትግላችንን አናቆምም፤ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን” ብለዋል።

በድጋፍ ርክክቡ ላይ የተገኙት በአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ እጅጉ ፥ “አገራችን ከውስጥ እና ከውጭ የተጋረጡባትን ጫናዎች ለመመከት የመከላከያ ሠራዊታችን የሚያደርገውን ተጋድሎ ለመደገፍ የከተማችን ኀብረተሰብ ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል” ብለዋል፡፡

የቦሌ ክፍለ ከተማም ለሠራዊቱ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከከተማዋ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.