Fana: At a Speed of Life!

የመዲናዋ ጤና ቢሮ ለሸደሆ መቄት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለሸደሆ መቄት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የመድሃኒትና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉን ያስረከቡት የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ሙሉጌታ እንዳለ እንደገለጹት÷ አሸባሪው ህወሓት ወርሯቸው በነበሩ ቦታዎች የጤና ተቋማትን አውድሟል፤ የንብረት ዘረፋም ፈጽመዋል፡፡
ድጋፉ የተገኘው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የህክምና ተቋማትንና መድሃኒት ቤቶችን በማስተባበር መሆኑም ነው ምክትል ኃላፊው የተናገሩት፡፡
ዘረፋና ውድመት የተፈጸመባቸው የጤና ተቋማት አገልግሎት ባለመስጠታቸው÷ በርካታ ዜጎች በተለያዩ በሽታዎች እየተሰቃዩ እና ለሞት እየተዳረጉ ነውም ብለዋል፡፡
ዜጎችን ከሞትና ከበሽታ ለመታደግ የህክምና ተቋማትን በፍጥነት በማቋቋም ወደ ስራ ማስገባት እንደሚገባም መመላከቱን ከመቄት ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የሸደሆ መቄት የመጀሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ይበልጣል ጌታ÷ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው፤ በሽብር ቡድኑ የጤና ተቋማት የደረሰባቸው ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.