ኢትዮጵያ ያጋጠማትን የውስጥ ችግር በመፍታት የቀደመውን የፖለቲካና ማህበራዊ ሁኔታ የማስቀጠል አቅም አላት- ባህራት ራጅ ፓውዲያል
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኔፓል የኢትዮጵያ አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ ከኔፓል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባህራት ራጅ ፓውዲያል ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በወቅቱም አምባሳደር ትዝታ በኢትዮጵያ እና ኔፓል መካከል እ.ኤ.አ በ1971 የሁለትዮሽ ግንኙነት መመስረታቸውን አውስተው÷ ሀገራቱ በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን መድረኮች በጋራ ጥቅሞቻቸው ላይ በቅርበትና በመተማመን መንፈስ የጋራ ትብብሮችን ሲያካሂዱ መቆየታቸውን አብራርተዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ግጭትን በማስቆም ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የወሰዳቸውን እርምጃዎች አስረድተው÷ በአንጻሩ የህወሓት የሽብር ቡድን ደግሞ የሰላም አማራጭን ባለመቀበል በወረራ በያዛቸው የአፋር እና አማራ ክልሎች ንጹሃንን መጨፍጨፉንም ነው ያብራሩት፡፡
አምባሳደር ትዝታ የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት ገልፀው÷ ኔፓል በባለብዙ መድረኮች ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ድጋፍ አጠናክራ እንድትቀጥልም ጠይቀዋል።
የኔፓል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባህራት ራጅ ፓውዲያል በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ግጭቱን በመፍታት የቀደመውን የፖለቲካና ማህበራዊ ሁኔታ የማስቀጠል አቅም እንዳላት ገልጸዋል።
የኔፓል መንግስት በሁለትዮሽ እና የባለብዙ መድረኮች በጋራ ጥቅሞች ዙሪያ በቅርበትና በትብብር ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነትም ማረጋገጣቸዉን ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!