Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሃት የአፋርን መሬት በመያዝ ለመደራደሪያ ለማቅረብ ማሰቡ መቀበሪያውን አፋጥኗል – አቶ አወል አርባ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሃት የአፋርን መሬት በመያዝ ለመደራደሪያ ለማቅረብ ማሰቡ መቀበሪያውን አፋጥኗል ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ተናገሩ፡፡
የደቡብ ክልል ለአፋር ክልል 52 ሚሊየን ብር የአይነት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፥ በዚህ ወቅት የሽብር ቡድኑ የአፋር አርብቶ አደርና የአማራ አርሶ አደሮችን መጉዳቱን፣ ሴቶች እናቶችን መድፈሩንና መግደሉ ተገልጿል፡፡
የሽብር ቡድኑ በማጥፋት የሚደሰት በመሆኑ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የሚገመት ሀብትን በክልሉ በማውደም በርካቶች እንዲፈናቀሉ አድርጓል ነው ያሉት አቶ አወል አርባ።
በደቡብ ክልል በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት አሰተባባሪ እና የመንገድ እና ትራንሰፖርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አበባየው ታደሰ ÷ ድጋፋን ሲያስረክቡ የሽብር ቡድኑ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የነበረው እቅድ የአፋር ህዝብ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር በመሆን በከፈሉት መስዋዕትነት መና ቀርቷል ብለዋል።
ክልሉ ያደረገው የአይነት ድጋፍም በሽብር ቡድኑ የጥፋት እጅ ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማገዝ እንደሚያስችል ተናግረው በቀጣይም ክልሉ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።
የአይነት ድጋፉ አልባስት፣ የስንዴ ዱቄት፣ ዘይት እና ለማብሰያ እና ለመመገቢያ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ይገኝበታል።
በበላይ ተስፋዬ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.