Fana: At a Speed of Life!

አርቲስት ታማኝ በየነና ደሳለኝ ሀይሉ ከግሎባል አሊያንስ ድርጀት ጋር በመሆን ለተፈናቃዮች 10 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስትና የማህበረሰብ አንቂው ታማኝ በየነ እና አርቲስት ደሳለኝ ሀይሉ ከግሎባል አሊያንስ ድርጀት ጋር በመሆን በጎንደርና አካባቢዋ ለሚገኙ ተፈናቃዮች 10 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የቁሳቁስ ድጋፍ አስረክበዋል፡፡
ድጋፉ የተደረገው በጦርነቱ ተፈናቅለው በእብናትና ደባርቅ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃይ ዜጎች ሲሆን÷ በአጠቃላይ 3 ሺህ ብርድ ልብስ፣ 3 ሺህ ፍራሽ እና 1 ሺህ 200 ኩንታል ዱቄት ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የተደረገው ድጋፍ በውጭ ሀገር ከሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተሠበሠበ ገንዘብ የተገዛ ነው ተብሏል፡፡
በኤሊያስ አንሙት
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.