Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች እና ለወደሙ ንብረቶች መልሶ ግንባታ የሚውል 23 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን በአማራ ክልል በአሸባሪው ህወኃት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ማቋቋሚያ እና ለወደሙ ንብረቶች መልሶ ግንባታ የሚውል 23 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፥ አሸባሪው ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ እና ህዝቦቿም የጉስቁልና ህይወት እንዲኖሩ ከሚጠቀምባቸው መሳሪያዎች አንዱ የኢኮኖሚው ግንባር መሆኑን ተናግረዋል።
ቡድኑ በዚህ ግንባር የሚያደርሰውን ጥፋት እና ሴራ ለማክሸፍ ኮሚሽኑ ከመቼውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አሸባሪው እና ዘራፊው ቡድን የአገር መከታ እና ኩራት በሆነው የመከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረሰው ጥቃት ከልባችን የማይጠፋ፣ በወረራ በያዛቸውም አካባቢዎች ያደረሰው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት መላው ኢትዮጵያውያንንም በእጅጉ ያሳዘነ ነው ብለዋል ኮሚሽነሩ፡፡
ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቤታቸው እስከሚመለሱ እና እስከሚቋቋሙ፣ በዘራፊው ቡድን የወደሙ ንብረቶችም የቀደመ አገልግሎታቸውን እስከሚሰጡ ድረስ ኮሚሽኑ የሚሰስተው ጉልበትም ሆነ ሀብት እንደሌለም ነው የተናገሩት፡፡
የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያውያን ተበተኑ ስንባል ተጠናክረን የምንቆም፣ ደከሙ ስንባል ጠላታችንን በአንድነት የምናሸንፍ ህዝቦች ስለመሆናችን በዘመቻው የታየው የትብብር መንፈስ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
አያይዘውም በክልሉ የደረሰው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጥፋት በምንም ለመተመን የማይቻል እና በአጭር ጊዜ ለመመለስ አስቸጋሪ መሆኑን አስረድተዋል።
ተፈናቃይ ወገኖችን ወደቀያቸው ለመመለስ እና የጠፉ ንብረቶችን ለመተካት በሚደረገው ጥረት መላው አገር ወዳድ ዜጋ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ ማቅረባቸውን የጉምቱክ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.