Fana: At a Speed of Life!

የጋሞ ዞን፣ በሐረሪ ክልል የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለተፈናቃዮች ድጋፍ አደረጉ

 

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋሞ ዞን፣ በሐረሪ ክልል የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለተፈናቃዮች ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የጋሞ ዞን በአሸባሪው ህወሓት ከአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች ከህዝቡ የተሰበሰበ 10 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብና 11 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የአይነት ድጋፍ ለክልሉ መንግስት አስረክበዋል።
የጋሞ ህዝብ ከአማራ ክልል ህዝብ ጎን በመቆም የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና አስተዳዳሪው አስታውቀዋል።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በበኩላቸው÷ “የተረከብነውን ድጋፍ ለተፈናቀሉ ወገኖች ማቋቋሚያና ለመልሶ ግንባታ እንዲውል በአግባቡ እናደርሳለን” ብለዋል።
በሌላ በኩል በሐረሪ ክልል በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለመከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቀሉ ወገኖች 2 ሚሊየን ብር የሚጠጋ የአይነት ድጋፍ እና 855 ማዳበሪያ አልባሳት ተሰበሰበ።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ መምህራንና ተማሪዎቹ ለአገራዊ ጥሪው ለሰጡት ምላሽና ተሳትፎ ምስጋና አቅርቧል።
የሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙኽታር ሳሊህ እንደተናገሩት እንደ አገር በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በክልሉ በሚገኙ የግልና የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና መምህራን ከአገራዊ ህልውና ጋር ተያይዞ ለአንድ ሳምንት የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውኑ ቆይተዋል።
በዚህም በተለይ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ እና በመጠየቅ፣ ደም በመለገስ፣ ስንቅ በማዘጋጀት እና ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ ማከናወናቸውን ተናግረዋል።
በዚህም በአጠቃላይ በክልሉ በሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች 2 ሚሊየን ብር የሚጠጋ የአይነት ድጋፍ እና 855 ማዳበሪያ አልባሳት መሰብሰቡን ገልፀዋል።
ተማሪዎቹና መምህራን ካከናወኑት ድጋፍ መካከልም 176 ማዳበሪያ ዳቦ ቆሎ ፣ በሶ ፣ ሩዝና ማካሮኒ እንዲሁም 105 ካርቶን ሰርዲን ፣ ቴምር፣ ወተት፣ ፓስታ፣ ዘይትና ብስኩት ይገኙበታል ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪም 85 ካርቶን የንፅህና መጠበቂያ፣ 855 ማዳበሪያ አልባሳት፣ 12 ብርድ ልብስ፣ 70 ካርቶን የመማሪያ ቁሳቁስ፣ 92 ካርቶን የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ እና በርካታ መጠን ያለው የቤት ቁሳቁስ ማሰባሰባቸውንም ነው የተናገሩት።
በክልሉ ሲሰጥ የቆየው የማህበረሰብ አገልግሎቱ ተጠናቆ በዛሬ እለት የመማር ማስተማር ስራ መጀመሩን ከሐረሪ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በተያያዘ በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍማሰባሰባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ”ዘመቻ ለህልውና በስዊዘርላንድ” በሚል መሪ ቃል ነው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ያካሄዱት።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.