Fana: At a Speed of Life!

ደቡብ አፍሪካ ከፍተኛውን የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ቁጥር አስመዘገበች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ደቡብ አፍሪካ በ24 ሰዓት ውስጥ ከፍተኛውን የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ቁጥር ማስመዘገቧ ተመለከተ።

ደቡብ አፍሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ ምርመራ 13 ሺህ 992 አዳዲስ የኮቪድ-19 ታማሚዎችን ማስመዝገቧ የተገለፀ ሲሆን ፥ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3 ሚሊየን 180 ሺህ 785 ደርሷል ነው የተባለው።

የተደረገው ምርምራ አጠቃላይ የአገሪቱን ህዝብ 31 በመቶ የሚወክል ሲሆን ፥ የአገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው ዘገባ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 90 ሺህ 148 ደርሷል ብሏል።

በአገሪቱ የተለያዩ ግዛቶች በተደረገው ምርመራ መሰረት ጋውቴንግ (48 በመቶ) እና ክዋዙሉ-ናታል (19በመቶ) በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን በማስመዝገብ ከፍተኛ ሆነው ተመዝግበዋል።

የብሔራዊ ጤና ላቦራቶሪ አገልግሎት ክፍል የሆነው (NICD) በደቡብ አፍሪካ የቫይረሱን ስርጭት በተመለከተ ምላሽ ለመስጠት አዲሱን የኦሚክሮን ቫይረስ ጨምሮ የተለያዩ ቤተ ሙከራዎችን በማድረግ ላይ መሆናቸውን የኤስቢሲ ዘገባ ያመለክታል።

የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎዛ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ራሳቸውን በማግለል የህክምና ክትትል እያደረጉ መሆናቸው ይታወሳል።

በሚኪያስ አየለ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.