አሸባሪው ህወሓት በደሴ ፋና ኤፍ ኤም ማሰራጫ ጣቢያ ላይ መጠነ ሰፊ ውድመትና ዘረፋ ፈጽሟል
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በደሴ ፋና ኤፍ ኤም ማሰራጫ ጣቢያ ላይ መጠነ ሰፊ ውድመትና ዘረፋ መፈጸሙ ተገለጸ፡፡
በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የደሴ ፋና ኤፍ ኤም ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሩ ከፈለኝ እንደገለጹት፥ አሸባሪው እና ወራሪው ህወሓት ከተማዋን በወረራ ይዞ በቆየበት ጊዜ ለህዝብ ልሳን የሆኑ የመገናኛ ብዙሃን መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ውድማት አድርሷል፡፡
መዳረሻውን ጥፋት አድርጎ በየደረሰበት ሁሉ ሰይጣናዊ ተግባሩን እያሳየ የሚገኘው የሽብር ቡድኑ ደሴ በሚገኘው ፋና ኤፍ ኤም ማሰራጫ ጣቢያ ላይም መጠነ ሰፊ ውድመትና ዘረፋ ፈጽሟል ነው ያሉት፡፡
ጣቢያው ከፊል ሰሜን ሸዋን፣ለአፋር እና ምስራቅ አማራ አካባቢ ለሚገኙ ዜጎች ወቅታዊ መረጃዎችን እንደሚያሰራጭ ነው ስራ አስኪያጁ የተናገሩት፡፡
አሸባሪው ቡድን ባደረሰው ውድመት ተቋሙን ከጥቅም ውጭ ከማድረጉም ባለፈ ዕቃዎቹን ለመተካት በሀገር ውስጥ መገኘት የማይችሉ እና ውድ በመሆናቸው ችግሩን ይበልጥ አሳሳቢ እንደሚያደርገው ጠቁመዋል፡፡
የክልል ጣቢያዎች ማስተባበሪያ ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ገመዳ በበኩላቸው÷የወደሙ ዕቃዎችን በሚቻለው ፍጥነት አስተካክሎ ጣቢያው ወደ ቀደመ ስራው እንዲመለስ እና መረጃዎችን ለማህበሰረቡ ተደራሽ እንዲያደርግ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
አሸባሪው ህወሓት በደሴ ቆይታው በከተማዋ በሚገኙ ሌሎች የመረጃ ምንጭ ተቋማት ላይ ተመሳሳይ ውድመት ማድረሱም ተመላክቷል፡፡
በይስማው አደራው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!