የተመድ ተወካዮች በአፋር ክልል ለተፈናቃይ ዜጎች እየተደረገ ያለውን ድጋፍ ተዘዋውረው ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 6፣2014(ኤፍ ቢሲ) በኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ እያቀረቡ የሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶችና አጋሮቹን ያካተተ ቡድን ዛሬ በአፋር ክልል ለተፈናቃይ ዜጎች እየተደረገ ያለውን ድጋፍ ተዘዋውሮ ጎበኘ።
በተመድ የኢትዮጵያ ፅህፈት ቤት አስተባባሪ ዶ/ር ካትሪን ሶዚ የተመራው ልዑኩ በአሸባሪው ህወሃት ወረራ ምክንያት ተፈናቅለው በመጠለያ የሚገኙ ዜጎች እያገኙት ያለውን ድጋፍ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በዚህም ወቅት በአካባቢው የሰብዓዊ እርዳታ እያቀረቡ ከሚገኙ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ውይይት ተደርጓል።
በውይይታቸውም ለተፈናቃዮች የሚቀርበውን የሰብዓዊ እርዳታ የበለጠ ማቀላጠፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ነው የተነጋገሩት።