በሀረሪ ክልል የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተፈፃሚ ሆኗል
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተፈፃሚ መሆኑን የክልሉ ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ቦርድ አስታቋል፡፡
የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የ2014 በጀት አመት የአባላት ምዝገባና እድሳት የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እንደገለጹት÷ የጤናው ዘርፍ ሀገራዊ ተልዕኮውን ከማሳካት ጎን ለጎን ለመከላከያ ሰራዊቱና በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች ዘርፈ ብዙ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የህብረተሰቡን የጤና ጥያቄ ለመመለስ የጤና ተቋማትን አቅም ማሳደግ፣ በሰው ሀይልና ግብዓት በማደራጀት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን የጤና ተቋማትን ክፍተት መድፈን ይገባል ብለዋል፡፡
በዘርፉ ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ በክልሉ የሚገኙ ወረዳዎች በዘርፉ ወጥ የሆነ አፈፃፀም ለማስመዝገብ በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበው÷ ለተመዘገበው ውጤት ባለድርሻ አካላቱን አመስግነዋል፡፡
የሀረሪ ክልል በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽነት በሀረሪ ክልል መቶ በመቶ መሳካቱን የገለፁት የፌደራል የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ኤጀንሲ ዳይሬክተር ፍሬህይወት አበበ÷ በክልሉ የተዘመገበው ውጤት በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደተሞክሮ ሊወሰድ የሚችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና በክልሉ የማህረሰብ አቀፍ ጤና መድን ቦርድ ሰብሳቢ ሚስራ አብደላ በበኩላቸው÷ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ለማህበረሰቡ ተደራሽ ከማድረግ አንፃር እያዳንዱ አመራር ሀላፊነቱን በመውሰድ ሊሰራ እንደሚገባና ሀላፊነታቸውን በአግባቡ የማይወጡ አመራሮቸ ተጠያቂ የሚደረግበት ሁኔታ ይራል ብለዋል፡፡
በዘርፉ ጥሩ አፈፃፀም ላመጡ ከገጠር ሶፊ እንዲሁም ከከተማ ሀኪም ወረዳ የማበረታቻ ሽልማት መበርከቱን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!