Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ ቴሌኮም መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር ለተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ ቴሌኮም መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ድጋፍ በደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮችና ለደብረ ብርሃን ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድጋፍ አድርጓል።
የማህበሩ ሊቀመንበር ካሳሁን ሰቦቃ እንደተናገሩት÷ ድጋፉ ሰራተኞች በየዲስትሪክቱ ካደረጉት ድጋፍ በተጨማሪ ከማህበሩ 3 ሚሊየን ብር ተመድቦ 1 ነጥብ 5 ሚሊየኑ በቀጥታ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ተደርጓል፡፡
በቀሪው 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ደግሞ ፍራሽ፣ የንፅህና መጠበቂያ እና የምግብ እህል በመግዛት ዛሬ በደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ አድርገናል ብለዋል፡፡
በአበበ የሸዋልዑል
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.