Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በመርሳ ከተማ የአእምሮ ህሙማንን ”ሰላዮች ናቸው” በሚል እያፈላለገ ገድሏል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በመርሳ ከተማ የአእምሮ ህሙማንን ”ሰላዮች ናቸው” በሚል እያፈላለገ መግደሉን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች በመርሳ ያልፈጸሙት ግፍ የለም፤ እንደ ሰው ቆመው ይሄዳሉ፤ ይናገራሉ እንጂ ድርጊታቸው ፈጽሞ የሰው አይደለም ሲሉ ነዋሪዎች ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡
የአእምሮ ህሙማንን ‘ለተልእኮ የተቀመጡ፣ መረጃ አቀባዮች ሰላዮች ናቸው’ በማለት በከተማው ያሉ የአዕምሮ ህሙማንን በያሉበት አሳደው ገድለዋቸዋል ብለዋል፡፡
የአዕምሮ ታማሚዎቹን ተገድለው አስከሬናቸውን አይተናል፤ ለሞቱት ማልቀስ ስለሚያስገድል በልባችን እያለቀስን ምንም የማያውቁትን ሰዎች ስድስት ሆነን ቀብረናል ብለዋል፡፡
ነዋሪዎቹ ወራሪው ሀይል በከተማዋ በቆየባቸው ወራት ንጹሃንን የመንግሥት ደጋፊ ናችሁ በማለት መግደሉን፣ በየቤቱ በመዞር ዝርፊያ መፈጸሙን ተናግረዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.