Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሃሙሲት ሴቶችን በቡድን ደፍሯል – ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሃት ቡድን በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ ሃሙሲት ከተማ በወረራ በቆየባቸው ጊዜያት እጅግ አሰቃቂ ግፍ ሲፈጽም መቆየቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
የአሸባሪው ህወሓት ቡድን አባላት በከተማዋ ሴቶችን በቡድን አስገድደው በመድፈር እንዲሁም ሰላማዊ ዜጎችን በጅምላ በመጨፍጨፍና ንብረት በማውደም ግፍ ፈጽመዋል፡፡
የዋድላ ሃሙሲት ከተማ ነዋሪዎች አሸባሪ ቡድኑ ወደ ከተማዋ ከገባበት እለት ጀምሮ የሰቆቃ ጊዜ እንዳሳለፉ ለመቄት ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ተናግረዋል፡፡
የሽብር ቡድ አባላት በርካታ ወጣቶችን በአደባባይ በግፍ ገድለዋል፤ ሴቶችን በቡድን ደፍረዋል፤ የግለሰቦችን ቤት በየቀኑ እየፈተሹ ሃብት ንብረት ዘርፈዋል” ነው ያሉት ነዋሪዎቹ፡፡
ቡድኑ የዋድላ ሃሙሲት ጤና ጣቢያን ጨምሮ የግብርና ጽ/ቤቱን እና ትምህርት ቤቶችን ዘርፏል፤ ሲሽሽም የሃሙሲት ጤና ጣቢያን በእሳት ለኩሶት መሄዱን ነው የተናገሩት፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.