Fana: At a Speed of Life!

የአርዳይታ ግብርና ሙያ ቴክኒክና ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ ማህበረሰብ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርዳይታ ግብርና ሙያ ቴክኒክና ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ ማህበረሰብ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ከ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የስንቅ ዝግጅት እና የደም ልገሳ መርሃ ግብር በማካሄድ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የመርሃ ግብሩ ተሳታፊዎች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት÷ አሸባሪዎቹን ህወሓት እና ሸኔን እየደመሰሰ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እያስከበረ ለሚገኘዉ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ደጀን መሆናችንን በድጋፋችን እናረጋግጣለን ብለዋል።
ስንቅ ማዘጋጀትና ደም መለገስ ብቻ በቂ ባለመሆኑም ልጆቻችንን ወደ ግንባር ልከናል፤ እኛም ከኋላ ዘምተን የህይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ሲሉ ገልጸዋል።
የኮሌጁ ዲን አዲሱ ወንድሙ እንደገለጹት÷ የኮሌጁ ማህበረሰብ በራሱ ተነሳሽነት ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ልጆቻቸውን መርቀው ወደ ግንባር ከመላክ ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን አድርገዋል፡፡
በሶስት ዙር ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ስንቅ፣ ሰንጋዎች፣ የፅዳት መጠበቂያና ሌሎችም ድጋፎችን ማድረጋቸውን አስረድተዋል፡፡
በቢቂላ ቱፋ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.