የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ ግብዓት ማሰባሰብ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቶ የተለያዩ ግብዓቶችን አሰባስቧል፡፡
በይፋዊ የውይይት መድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እና የተለያዩ የሲቪክ ማህበራት የስራ ኃላፊዎች መሳተፋቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በውይይቱ መግቢያ ላይ የፍትህ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዮስ÷ ማቋቋሚያ አዋጁን አስመልክተው ባቀረቡት ገለጻ የማቋቋሚያ አዋጁን አስፈላጊነት፣ እስካሁን ያለፈባቸውን ሂደቶች እንዲሁም የኮሚሽኑ ተግባርና ኃላፊነትን አብራርተዋል፡፡
ለአገራዊ መግባባት የሚጠቅሙ አጀንዳዎችን መለየት፣ የሚሳተፉ አካላትን መለየት፣ የምክክር መድረኮችን ማሳለጥ፣ ከምክክር መድረኮቹ የተገኙ ምክረ ሀሳቦችንና የአተገባበር ስልታቸውን የሚጠቁም ሰነድ ማዘጋጀት እንዲሁም ተግባራዊነታቸውን መከታተል ከሚቋቋመው ኮሚሽን የሚጠበቁ ዋና ዋና ተግባራት ስለመሆናቸውም ጠቁመዋል፡፡
በሚቋቋመው ኮሚሽን ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም የኮሚሽነሮች አሰያየም ላይ ተደጋጋሚ አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን÷ በረቂቅ አዋጁ አንቀጽ 9/10 ስር ኮሚሽኑ ዝርዝር ሪፖርት በማዘጋጀት ለመንግስት ያቀርባል የሚለው ሀሳብ ኮሚሽኑን በመንግስት ተጽእኖ ስር ሊከተው ይችላል የሚሉና የገለልተኝነት ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!