Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደሴ ዲስትሪክት ከ80 በላይ ትራንስፎርመር በአሸባሪው ህወሓት ተዘርፏል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደሴ ዲስትሪክት ከ80 በላይ ትራንስፎርመር በአሸባሪው ህወሓት ተዘርፏል፡፡
በአማራ ክልል ከተዋቀሩ 6 ዲስትሪክቶች መካከል አንዱ የሆነው የደሴ ዲስትሪክት÷ በስሩ 23 የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት አሉት።
የደሴ ዲስትሪክት ዳይሬክተር ሀብቱ አበበ እንደገለጹት÷ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች በደረሱባቸው ቦታዎች የሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የሽብር ቡድኑ በዲስትሪክቱ ዋና መስሪያ ቤት ያሉ ንብረቶችን የቻለውን ዘርፎ ቀሪውን ሙሉ በሙሉ አውድሞ መሄዱን ገልጸዋል።
ከከባድ ተሽከርካሪ ጀምሮ በማከማቻ ማዕከሉ ውስጥ የሚገኙ ንብረቶችን ዘርፎና አውድሞ ተቋሙን ባዶ አድርጎታል ብለዋል።
በደሴ ዲስትሪክት በዋናው የክምችት ማዕከል የሚገኙ በሚሊየን ብር የሚቆጠር ግምት ያላቸው ከ80 በላይ ትራንስፎርመሮች እንደተዘረፉም ነው የተናገሩት።
የሽብር ቡድኑ የኢንዱስትሪ ማዕከል የሆኑት የደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች የመብራት እጦት እንዲገጥማቸው ለማድረግ የደሴን ሰብ ስቴሽን (ማከፋፈያ) ጣቢያ በከባድ መሳሪያ መድፍ እንዳወደመውም አስረድተዋል።
በደሴ ዲስትሪክት ላይ የተፈጸመው ዘረፋና ውድመት ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት አቶ ሀብቱ÷ይሄንን በአዲስ መልክ ለማደራጀት እንገደዳለን ብለዋል።
በመሆኑም የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን የፌደራሉ ጭምር ተቀናጅተው ይፈቱታል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.