ወደ ሀገር ቤት ለሚመጡ ዳያስፖራዎች በቂ የደህንነት ጥበቃ እንደሚደረግላቸው ጥምር የፀጥታ ኃይሉ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጥሪ ተከትሎ ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያለምንም የፀጥታ ችግር መንቀሳቀስ እንዲችሉ በቂ የደህንነት ጥበቃ እንደሚደረግላቸው በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመው ጥምር የፀጥታ ኃይል አስታወቀ፡፡
ከሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ከሪፐብሊካን ጋርድ፣ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ፣ ከኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት የተውጣጣው ጥምር የፀጥታ ኃይል ሀገራዊ የፀጥታ ሁኔታን በገመገመበትና ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡
በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት በሚመጡበት ጊዜ ያለምንም የሰላምና የፀጥታ ስጋት በፕሮግራማቸው መሰረት መንቀሳቀስ እንደሚችሉና ያለው የፀጥታ ሁኔታም አስተማማኝ መሆኑን ጥምር የፀጥታ ኃይሉ ገልጿል፡፡
ጥምር የፀጥታ ኃይሉ በአጠቃላይ ያለውን ሀገራዊ የፀጥታ ሁኔታ ገምግሞ በቂ ዝግጅት አድርጎ ወደ ስምሪት መግባቱንም የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!