Fana: At a Speed of Life!

ቻይና እስካሁን 5 ሚሊየን የኮቪድ-19 ክትባት ለኢትዮጵያ ለግሳለች  

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና እስካሁን 5 ሚሊየን የኮቪድ-19 ክትባትን ለኢትዮጵያ መለገሷን ገለፀች።

በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ፥ 5 ሚሊየን ክትባት ከመለገስ ባለፈም ኢትዮጵያ በግዢ የኮቪድ -19 ክትባትን እንድታገኝ የማመቻቸት እና በኮቫክስ ማእቀፍ በኩልም 2 ሚሊየን የሚጠጋ ክትባት እንድታገኝ መደረጉን ነው ያመለከተው።

መግለጫው በቅርቡ በተካሄደው የቻይና አፍሪካ መድረክ ላይ ፕሬዚዳንት ሺ ጂን ፒንግ በቀጣይ 1 ቢሊየን የኮቪድ-19 ክትባት ለአህጉሪቱ እንደምትሰጥ ቃል ገብተው እንደነበር አስታውሷል።

ቻይና የገባችውን ቃል ትጠብቃለች ያለው መግለጫው፥ በኢትዮጵያ የበሽታው ወረርሽኝ እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ የፕሬዚዳንቱን ቃል በፍጥነት በመተግበር ሀገሪቱ ክትባቱን ቶሎ እንድታገኝ ይደረጋል ብሏል።

ይህም ድጋፍ ኢትዮጵያ የበሽታውን ስርጭት እንድትቋቋም የሚያስችላትን አቅም እንደሚፈጥርላት ነው ያመለከተው።

በአጠቃላይ ቻይና በገባችው ቃል መሰረት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአፍሪካ አገራት ክትባት መለገሷን እንደምትቀጥል ኤምባሲው አረጋግጧል።

ቻይና እስካሁን ለ120 ሀገራት 2 ቢሊየን የሚጠጋ ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባትን ለግሳለች። ይህም ሀገሪቱ ከፍተኛ መጠን ያለው የክትባት መጠን በመለገስ ቀዳሚ ሀገር ያደርጋታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.