በኮምቦልቻ እና ደሴ ጉዳት የደረሰባቸውን ኢንዱስትሪዎች መልሶ ለማቋቋም ጊዜያዊ ቢሮ ተከፈተ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪው እና ወራሪው ህወሓት ቡድን ኮምቦልቻና ደሴ ከተሞች ላይ ያወደማቸውንና ጉዳት ያደረሰባቸውን ኢንዱስትሪዎች መልሶ ለመቋቋም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጊዜያዊ ቢሮ ከፍቷል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአሸባሪ ቡድኑ ጉዳት የደረሰባቸውን ኢንዱስትሪዎች የመጀመሪያ ዙር አጥኚ ቡድን በቦታው ልኮ የጉዳቱን መጠን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
ጥናቱን መነሻ በማድረግ ኢንዱስትሪዎቹን መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል የቅርብ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ በኮምቦልቻ ከተማ ጊዜያዊ ቢሮ በመክፈት ሰራተኛ መድቦ ወደ ተግባር መግባቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ቢሮው የተከፈተው በኮምቦልቻ ብረታ ብረት ምርቶች ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ግቢ ውስጥ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ስለሆነም ማንኛውም የኢንዱስትሪ ባለቤት ወደ ጊዜያዊ ቢሮው በመምጣት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችል ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡
አሸባሪው ህወሓት በደሴ እና ኮምቦልቻ በሚገኙ 40 ፋብሪካዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን በጥናት መረጋገጡን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል÷ስምንት ፋብሪካዎች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው እና እነዚህ ፋብሪካዎችበአጭር ጊዜ እንደማይመለሱ ተናግረዋል፡፡
ስምንቱ ደግሞ መካከለኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ጠቅሰው፥24 የሚሆኑ ፋብሪካዎች ደግሞ ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው ብለዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!