የጤና መረጃ ጥራትን ከማስጠበቅ እና የመረጃ አጠቃቀምን ከማሻሻል አኳያ ያለው አሰራር አበረታች ነው ተባለ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር የጤና መረጃ ጥራትን ከማስጠበቅ እና የመረጃ አጠቃቀምን ከማሻሻል አኳያ ያለው አሰራር ሊበረታታ የሚገባው ስርዓት መሆኑን የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ አስታወቁ።
የጤና ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የ100 ቀን እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል።
በዚህ ወቅት ሚኒስትሯ የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል እየተተገበሩ ያሉ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች መልካም መሆናቸውን ጠቅሰው፥ በቀጣይም ፍትሐዊና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለማድረስ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር፣ የድጋፍና የክትትል ስርዓትን ማጎልበት፣ የጥናትና ምርምር ስራዎች ላይ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ሚኒስቴሩ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ላይ የወሰዳቸው የመከላከያ እርምጃዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን ገልጸው፥ በቀጣይም እንደ አገር ጠንካራ እና በወረርሽኝ የማይበገር የጤና ስርዓት መፍጠር ላይ መረባረብ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በተጨማሪም የጤና መረጃ ጥራትን ከማስጠበቅ እና የመረጃ አጠቃቀምን ከማሻሻል አኳያ ያለው አሰራር መልካም መሆኑን ጠቁመው፥ የስራ አካባቢን ምቹ ከማድረግ አኳያም የተሰሩ ስራዎች ጠንካራ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
ከክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች እንዲሁም ከተጠሪ ተቋማት እና ከሆስፒታሎች ጋር የተዘረጋው ቅንጅታዊና ተዋረዳዊ አሰራር ጠንካራ እና የተናበበ በመሆኑ ሌሎች ተቋማትም በተሞክሮነት በመውሰድ ለውጤታማነት ሊሰሩበት ይገባል ማለታቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የምግብና መድኃኒት ቁጥጥርን ማጠናከር ፣ የጤና ፋይናንስ ስርዓቱን ይበልጥ ማጎልበት፣ የመድኃኒት አምራች ኢንዱስትሪዎችን ማበረታታት እንዲሁም በጤና ተቋማት የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶች ተገልጋይ ተኮር አድርጎ ጥራትና ፍትኃዊነትን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ሊሰጥ ይገባልም ነው ያሉት።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!