Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የፌዴራል እና የክልል መንግስታት የህግ አስፈጻሚዎች የግንኙነት መድረክ በሰመራ ተጀመረ

 

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የፌዴራል እና የክልል መንግስታት የህግ አስፈጻሚዎች የግንኙነት መድረክ በሰመራ ዛሬ ተጀምሯል ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች በመድረኩ ተገኝተዋል።

መድረኩ በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክርም ነው የተገለፀው ።

ጥቅምት ወር ላይ ባህር ዳር በተካሄደው የፌዴራልና የክልል መንግስታት የህግ አስፈፃሚዎች መድረከ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አፈጻጸምን ይገመግማል ።

እንደዚሁም ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታን ገምግሞ  ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ነው የሚጠበቀው ።

 

በአልአዛር ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.