Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በአስከፊ ሁኔታ እየተሰፋፋ ስለመጣ ሁሉም ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር በኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከል ዙሪያ ከጤና ማህበራዊ ልማት ፣ ከባህልና ስፖርት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና አባላት እንዲሁም ከሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጋር በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት አድርጓል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በውይይቱ ላይ ፥ አሁን ባለው መዘናጋት ምክንያት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋና በየጊዜው እራሱን እየቀያየረ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ እያደረሰ ነው ብለዋል።

በመሆኑም መደበኛ የመከላከያ ዘዴዎችንና ክትባቱን በአግባቡ በመውሰድ ህብረተሰቡ ሳይታክት ተግባራዊ እንዲያደርግ ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰራት እንዳለበት ተናግረው፥ የምክር ቤት አባላቱም ህብረተሰቡን የማንቃት እና ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ እንዲያከናውኑ ብለዋል።

ሚኒስትሯ አያይዘውም ህብረተሰቡን ከአስከፊው የኮቪድ ወረርሽኝ ለመጠበቅ የተለያዩ እርምጃዎችን ሲወስድ መቆየቱን አስታውሰው፥ በቀጣይም የመከላከሉን ሥራ ውጤታማ ለማድረግ በክትባቱ ዙሪያ የሚወሩ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ፣ አሉባልታዎችን እና ኢ-ሳይንሳዊ የሆኑ መረጃዎችን ወደ ጎን በመተው በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥራታቸው የተረጋገጠ ክትባቶችን በመውሰድ ጤንነቱን መጠበቅ ይገባዋል ብለዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ በበኩላቸው ፥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን አበረታች ስራ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታትና ለመቆጣጠር በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ስነ -ልቦናዊ ላይ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በትብብር በመስራት የበሽታውን የመከላከያ መንገዶችንና ክትባቱን ያለመሰላቸት ማህበረሰባችን እንዲተገብር መስራትና አገራዊ ኃላፊነታችንን በከፍተኛ ደረጃ ልንወጣ ይገባል ማለታቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.