በኢትዮጵያ በ24 ሰዓት ውስጥ 5 ሺህ 13 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በኢትዮጵያ በ24 ሰዓት ውስጥ 5 ሺህ 13 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ ባወጣው ዕለታዊ መረጃ በ24 ሰዓት ውስጥ 14 ሺህ 27 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 5 ሺህ 13 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አስታውቋል፡፡
እንዲሁም 6 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
በአንፃሩ 106 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገም ችለዋል፡፡
በኢትዮጵያ እስከአሁን ለ4 ሚሊየን 41 ሺህ 996 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል፡፡