Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በደሴ ከተማ ጎልደን ጌት ሆቴል ላይ 40 ሚሊየን ብር የሚገመት ሃብት አውድሟል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው እና ወረሪው የህወሓት ቡድን በደሴ ከተማ በሚገኘው ጎልደን ጌት ሆቴል ላይ ግምታዊ ዋጋው 40 ሚሊየን ብር የሚደርስ ሃብት ማውደሙ እና መዝረፉ ተገለጸ።
 
ቡድኑ በደሴ ከተማ በወረራ በቆየባቸው ጊዜያት ከዘረፈው ሃብት በተጨማሪ በውስጡ የሚገኙ ቁሳቁሶች አገልግሎት እንዳይሰጡ አድርጎ አውድሟል።
 
በተጨማሪም የሽብር ቡድኑ በሆቴሉ ውስጥ የነበሩ ልዩ ልዩ ሰነዶችን ቀዶ በማቃጠል አስነዋሪ ድርጊት ፈጽሟል።
 
ዘራፊው እና ወራሪው ቡድን ሙያዊ እውቀት የሚፈልጉ የመገልገያ እቃዎችንም በጀሌ ባለሙያዎቹ እየታገዘ መዝረፉ ነው የተገለጸው።
 
በለይኩን ዓለም
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.