Fana: At a Speed of Life!

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ፋግታ ለኮማ ወረዳ በአሸዋ ቀበሌ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በ3 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።

አደጋው ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከቲሊሊ ወደ ባህር ዳር ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ዶልፊን ከዳንግላ ወደ አዲስ ቅዳም ሲጓዝ ከነበረ የጭነት አይሱዚ መኪና ጋር በመጋጨቱ የደረሰ ነው፡፡

በአደጋውም የአንድ ሰው ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በ3 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳትና በስድስት ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የፋግታ ለኮማ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.