ዩኒቨርሲቲዎች የዳያስፖራውን ወደ ሀገር ቤት መምጣት ለመልካም አጋጣሚ ሊጠቀሙበት ይገባል- ምሁራን
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ዩኒቨርሲቲዎች የዲያስፖራውን ወደ ሀገር ቤት መምጣት ለመልካም አጋጣሚ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ምሁራን አመላከቱ፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው ምሁራኑ፥ ዳያስፖራዎች ለመጪው ገና በዓል ወደ ሀገር ቤት መግባታቸው ለዩኒቨርሲቲዎች የልምድና ዕውቀት መቀመሪያ ዕድልን ይጥል ብለዋል፡፡
በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና አለምአቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪው ሱራፌል ጌታሁን፥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በኮቪድ 19 የተዛባውን የመማር ማስተማር ሂደታቸውን ምሁራን ዳያስፖራዎችን በመጠቀም ሊያስተካክሉ እንደሚችል ጠቁመዋል።
በአሸባሪው ህውሓት የወደሙ ዩኒቨርሲቲዎችን መልሶ ለማቋቋም ሰፊ የሰው ሃይልና ምጣኔ ሀብት እንደሚያስፈልግ የተናገሩት ምሁሩ፥ የዳያስፖራውን እውቀትና ገንዘብ መጠቀም ከተቻለ ችግሩን በአጭር ጊዜ መፍታት ይችላል ብለዋል።
በዩኒቨርሲቲው መምህር የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ሻንበል ቱፋ በበኩላቸው፥ የዳያስፖራዎቹ ወደ ሀገር ቤት መግባት የምሁራንን መቀራረብ ያጎለብታል ብለዋል፡፡
ይህንንም መቀራረብ በመጠቀም ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምሁራን የሀገራቸውን ተጨባጭ ሁኔታ ለተቀረው ዓለም ማስተዋወቅ እንደሚጠበቅባቸውም አመላክተዋል፡፡
የምሁራኑ ተቀራርቦ መስራት በተናጠል ይደረግ የነበረው የበቃ ንቅናቄ በምሁራን የሚመራ ሊያደርገው እንደሚችልም ነው የገለጹት፡፡
የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የዳያስፖራዎችን ልምድና ዕውቀት ለመጋራት ዝግጁ መሆኑንን የተናገሩት ደግሞ በዩኒቨርሲቲው ጥናት ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ሰለሞን ዘሪሁን ናቸው።
በሀገር ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም በአከባቢያቸው የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ሰፊ ገለፃን ለዳያስፓራዎች ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
ይህም ዳያስፖራው የኢንቨስትመንት አማራጮችን በቀላሉ በመመልከት በሀገሩ ጥሪቱን እንዲያውል ያስችለዋል ብለዋል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!