Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ለመቀነስ ያለመ ውይይት በጎንደር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስ በኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ህይወት ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ለመቀነስ ያለመ ውይይት በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
 
ውይይቱ ኮቪድ-19ን ለመከላከል ድንበር ተሻጋሪ ስራዎችን ለመስራት በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስት /ኢጋድ/ እና የአውሮፓ ህብረት መሰራት ስላለባቸው ጉዳዮች ሀሳብ ተነስቷል።
 
ድንበር ተሻጋሪ ኮሜቴው በሱዳን እና በኢትዮጵያ ድንበሮች እንዲሁም በመተማ የድንበር አካባቢዎች ሊሰሩ ስለሚገባ የኮሮና ቫይረስ መከላከል ስራዎች ውይይት እየተደረገም ነው።
 
ኮቪድ-19ን ለመከላከል ድንበር ተሻጋሪ ኮሜቴው በሀገራት መካከል የመከላከል ስራዎችን የኢጋድ የኮቪድ ምላሽ አስተባባሪ ዶክተር ግሩም ሀይሉ ተናግረዋል።
 
በስምንቱ የኢጋድ አባል ሀገራት መካከል ድንበር ተሻጋራ ኮሜቴዎች ኮቪድን ለመከላከል ድጋፍ እንዲያደርጉም ተናግረዋል።
 
እንደነዚህ አይነት ድንበር ተሻጋሪ ኮሜቴዎች ኮቪድን ለመከላከል በድንበር ያልታጠረ ስራዎችን ለመስራት ይረዳል ያሉት ደግሞ በምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስት ኢጋድ የመተማ መግቢያ እና መውጫ አስተባባሪ አቶ መለሰ ማስሬ ናቸው።
 
በኢትዮጵያ ህብረተሰቡ ጤና ኢንስትቲዩት የጉዞ እና የድንበር ጤና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዮሐንስ ዱጉሳ በበኩላቸው፥ ድንበር ተሻጋሪ ስራዎች መሰራታቸው እየተስፋፋ የመጣውን የኮቪድ ወረርሽኝ ለመከላከል ሚናው ከፍ ያለ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
 
የሰዎች እንቅስቃሴ ፈጣን በሆነበት በዚህ ዘመን የሰው ልጆችን ችግር ድንበር አጥሮ መፍታት የሚቻል ባለመሆኑ እንደነዚህ አይነት ስራዎችን በአንክሮ መስራት ይገባልም ነው ያሉት።
 
 
በክብረወሰን ኑሩ
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.