ኤጀንሲው በመረጃ ደህንነት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ጋር ተፈራረመ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የዘመናዊ ግብይት ስርዓትን ለማሳለጥ በሚያግዙ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና በመረጃ ደህንነት ዘርፍ በጋራ ለመስራት ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ጋር ተፈራርሟል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በአዋጅ ከተሰጡት ሃላፊነቶች ዋናው የሃገሪቱን የኢንፎርሜሽን መሰረተ ልማት ደህንነት ማስጠበቅ መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው ተናግረዋል፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ምርት ገበያ አይነት ወሳኝ ሃገራዊ ተቋምን ደህንነት ማረጋገጥ የኤጀንሲው ቀዳሚ ተግባር ነውም ብለዋል።
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የመረጃ ፍስት እንዳይስተጓጎል ደህንነቱን ጠብቆ እንዲዘዋወር ማድረግ ይገባል ያሉት ዳይሬክተሩ÷ የመረጃን ወሳኝ ሃብትነት በመረዳት የኢትዮጵያ ምርት ገበያን በሚያስፈልገው ሁሉ ተቋሙ ከጎናቸው እንደሚሆን ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድማገኝ ነገራ በበኩላቸው፥ ተቋሙ ከኤጀንሲው ጋር ለመስራት መፈራረሙ ለያዘው የአፍሪካ የልህቀት ማዕከልነት ግስጋሴ እና ምርት ገበያው ወደፊት ለሚጀምራቸው ወሳኝ ስራዎች የቴክኖሎጂ አቅምን እና ብቃትን ለማጎልበት የላቀ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከ25 ሚሊየን ህዝብ በላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሚደረጉ የግብይት ስርዓቶች ተጠቃሚ እንደሚሆን እና በየአመቱ 40 ቢሊየን ብር ዋጋ ያላቸውን ምርቶች እንደሚያገበያይ መግለጻቸውን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!